አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ ለኩባንያው አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ነገሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 05/2018
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ ለኩባንያው አገልግሎት የሚውሉ፡-
· ሎት 1 የተለያዩ የጽህፈትና የጽዳት ዕቃዎችን
· ሎት 2 የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮችን
· ሎት 3 የተሽከርካሪ ጎማና ጌጣጌጦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለሎት 1 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር)፣ ለሎት 2 ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) እና ለሎት 3 ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ፣ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች ከኩባንያው ጋር ውል በመግባት አጓጉዘው በኩባንያው የንብረት ማከማቻ መጋዝን ገቢ ማድረግ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ፋይናሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው በ13/6/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢማ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
7. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ህንጻ ጎን
ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር፡- 011-1-26-38-88 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ
