Tender Detail

Tender Details


የቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የስልጠና ማቴሪያልና ሌሎችንም ልዩ ልዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የ2018 ዓ/ም ለሁስተኛ ጊዜ የወጣ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የስልጠና ማቴሪያልና ሌሎችንም ልዩ ልዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡- 1. ለጀነራል መካኒክ፣ 2 ለአውቶ መካኒክ፣ 3. ለኤሌክትሪሲቲ፣ 4. ለኮንስትራክሽን ቴከኖሎጂ፣ 5. ለጋርመንት፣ 6. ለአይሲቲ፣ 7. ለሰርቬይንግ፣ 8. ለድራፍቲንግ፣ 9. ለፈርኒቸር፣ 10. ለአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ 11. ለሆቴል ቱሪዝም፣ 12. ሳኒተሪ ኢንስታሌሽን፣ 13. ኢንዱስትሪያል ማሽነሪ እና የጽህፈት መሳሪያ የስልጠና ዘርፍ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች

1.በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው በፋይናንስ የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ከፋይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃዎችን ከዋናው ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. የእቃዎቹን ዝርዝር መግለጫ (Specification) የያዘ የጨረታ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለıo (ለአስር) ተከታታይየስራ ቀናት ቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡

3. የሚጫረቱባቸውንእቃዎች በመለየት በአይነታቸው የሚሸጡባቸውን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱባቸውን ዘርፍና _ የተጫራቹን ስም በግልጽ በመጻፍ የድርጅቱ ማህተም አርፎበት በጋዜጣ ከወጣበት በ15 (በአስራ አምስተኛው) ቀን ሰነዱን በገዙበት ኮሌጅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡

4. የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና ብር 10,000 (አስር ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) ከጨረታው ማወዳደሪያ ሰነድ ጋርማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. በጨረታው የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡

ገ 7. አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን መስሪያ ቤቱ በወሰነለት ቀን ካላቀረበ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስለትም፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡

9. ማሰልጠኛ ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡

10. እቃዎችን አሸናፊ ድርጅቶች ቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

11. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0461150655/0912470011/0910036765

የቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ   

Save Tender