በጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የላውንደሪ ማሽን፤ የህሙማን አልጋ፤ የላብራቶሪ ሲቢሲ ማሽን፤ የኦፕሬሽን ላይት ሲሊንግ ታይፕ የአጥንት ህክምና እና ለሎች የህክምና መሳሪያዎች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሠራተኞችን ደንብ ልብስ (ለማሰፋት) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የላውንደሪ ማሽን፤ የህሙማን አልጋ፤ የላብራቶሪ ሲቢሲ ማሽን፤ የኦፕሬሽን ላይት ሲሊንግ ታይፕ የአጥንት ህክምና እና ለሎች የህክምና መሳሪያዎች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሠራተኞችን ደንብ ልብስ (ለማሰፋት) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ
1. ንግድ ፍቃድ ያለው
2. የዘመኑ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
3. የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችል
4. የአቅራቢነት (PPT) የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
6. 2018 ዓ.ም የመንግስት ግብር የከፈለበት ከግብር ነፃ (Tax clearance) ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
7. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) ያለው፤
8. ከመቶ 3% (ዊዝሆልዲንግ) ግብር መክፈል የሚችል
9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ተጫራቾች ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ መግዥያ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ።
10. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡትን የጠቅላላ ዋጋ 1% ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ዶክመንታችሁን 1 (አንድ) ዋናውን እና 1 (አንድ) ኮፒ አንድ /1/ እና ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ አንድ /1/ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30-4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወደም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል ጊቢ ይከፈታል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0471513042 / 0911591960 ይጠቀሙ።
የጋም/ህ/ብ/ክ/መንግስት የጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል
