በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሶስተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ፣ ሎት 1 ደንብ ልብስ፣ ሎት 2 ሕትመት፣ ሎት 3 የህፃናት መጫወቻ ግብአቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መ/ቁ 03/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሶስተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ፣ ሎት 1 ደንብ ልብስ፣ ሎት 2 ሕትመት፣ ሎት 3 የህፃናት መጫወቻ ግብአቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ
2. በመስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደስ ንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እና የግብር መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ከወሰዱት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ በሌላ ሞልቶ ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ 4፡00 ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 35 የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
8. በጨረታው ለመሳተፍ ለእያንዳንዱ ሎት 4,000.00 /አራት ሺ ብር/ የተረጋገጠ የዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በማለት ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. ዘግይተው የቀረቡ የመወዳደሪያ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ወደ ፊትም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
11. በጨረታው ተወዳድሮ ያሸነፈውን እቃ በኮሌጁ ጥራት /ቴክኒክ ኮሚቴው ጥራቱ ሲረጋገጥ ተጫራቹ በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ በኮሌጁ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
12. ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ ቢያንስ ለ60 ቀናት መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል/
13. ት/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን እቃ ወይም አገልግሎት ብዛት መጠን እንደአስፈላነቱ እስከ 25 በመቶ ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብት ይኖረዋል፡፡
14. የዳ/ም 2ኛ/ደ/ት/ቤት ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
15. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ማግኘት ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 0111-54-57-56 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- 4 ኪሎ ዩኒቨርሲት ጎን
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
