ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የተረፈ ምርት የእንጨት ፍቅፋቂ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሳጋ ቱራ/የእንጨት ፍቅፋቂ/ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሆቡማማ/06/18
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የተረፈ ምርት የእንጨት ፍቅፋቂ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሙሉ ከታች የተዘረዘሩትን በማሟላት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ቲን ቁጥር ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
2. ለጨረታው ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 14 መግዛት ይቻላሉ፡፡
3. ለጨረታው ማስከበሪያ በሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር /HORIZON PLANTATIONS PLC/ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላየተ.የግል ማኅበር ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመገኘት የሳጋቱራውን ሳንፕል በማየት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የጨረታው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታ መዝጊያ ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
1 |
የእንጨት/የጣውላ ፍቅፋቂ (ሰጋቱራ) |
10,000 |
የካቲት 23/6/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ |
የካቲት 23/6/2018 4፡15 ይከፈታል |
5. ተጫራቾች የ1ኪ.ግ ዋጋ ቫትን በመጨመር የሰራተኛና የትራንስፖርት ዋጋ አካተው ድርጅቱ ድረስ የሚያቀርቡበትን ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
7. ጨረታው ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ3 /ሶስስት/ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የሥራ ውል ተፈራርሞ ሥራውን መጀመር ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታው ያሲያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 442 37 24
ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኃላ.የተ.የግል ማህበር
ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ድርጅት አድራሻ፡- ቅ/ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ብሔረፅጌ መናፈሻ በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር
