በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልጠና ማዕከል በ2018 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ድርጅቶች ግዥ መግዛት ይፈልጋል።
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር እ.አ.ስ.ስ.አ.ኮ.ስ.ማ 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልጠና ማዕከል በ2018 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ድርጅቶች ግዥ መግዛት ይፈልጋል ፤
ሎት 1- የምግብ ዝግጅት ግብዓቶች ምርት ግዥ፣
ሎት 2፡-የአላቂ የጽዳትና የቢሮ ዕቃዎች ግዥ፣
ሎት 3፡-የምግብ ማብሰያና መመገቢያ እቃዎች ግዥ፤
ሎት 4፡-የሰልጣኞችና የሰራተኞች መዝናኛ ካፌ የፊኒሽንግ ስራ፤
ሎት 5፡-የኤሌከትሮኒከስና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ
ሎት 6፡- የእሳት አደጋ ጠቋሚ መሳሪያዎች ግዥ ሲሆኑ
በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1.በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዘገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምስከር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIn) ምስክር ወረቀት ግብር ከፋይነትን የሚያረጋግጥ ከሀገር ውስጥ ገቢ ሰርተፍኬት (ታከስ ከሊራንስ) እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
2.የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 500/ አምስት መቶ ብር/በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ድረስ ብቻ አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራርኮሚሽን ስልጠና ማዕከል አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 1 ከፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላል::
3. ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 11 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ
ስልጠና ማዕከሉ ግዥ ክፍል ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4.ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ስልጠና ማዕከሉ አዳራሽ ይከፈታል፤ እለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
5.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልጠና ማዕከል ስም የተዘጋጀ የገንዘብ መጠን ከ ሎት 1 እስከ ሎት 2 ላሉት ብር 10,000.00 ( አስር ሺህ ብር) ሲሆን ለ ሎት 3 እስከ ሎት 6 ደግሞ 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6.ተጫራቾች የቴከኒከና ፋይናንሽያል ሰነዶች ተለይተው በተለያየ ፖስታ ፋያናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴከኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ በአራት ፖስታ በማድረግ ኮፒ እና ኦርጅናሉ በጉልህ ተጽፎ መቅረብ ይኖርበታል የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ኦርጅናል ስነድ ጋር በአንድ ላይ ታሽጎ መቅረብ አለበት::
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስታዲየም ጎን ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0114397220/0114399530 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ::
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልጠና ማዕከል
