Tender Detail

Tender Details

  • Company CITY GOVERNMENT OF ADDIS ABABA TRADE BUREAU (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ)
  • Address ውቤ በረሃ ደጃች ውቤ 1888 ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118126179
  • Websitehttps://aacatb.gov.et/
  • Deadline05 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-03-05 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Services , Marketing

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሎት 1 የደንብ ልብስ ግዢ እና ሎት 2 የገበያ ጥናት ትንቢያ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም ይፈልጋል።


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ

ማስታወቂያ ቁጥር 03//2018

 

የግዢው አይነት

ሎት 1 የደንብ ልብስ ግዢ

ሎት 2 የገበያ ጥናት ትንቢያ

 

1.     በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያለውና 2018 የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ ያላቸው።

2.     ለዕቃ አቅራቢነት ስለመመዝገባቸው እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3.     የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ስም CPO (ጋራንት ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ የሚችሉ።

4.     የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

5.     ይህ የጨታ ማስታቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

6.     ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ቢሮው በሰጣችሁ ፎርማት ላይ በመሙላት እና የድርጅታችሁ ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ።

6.1.          ፋይናንሽያል አንድ ጅናል እና እና ፋይናንሽያል አንድ ኮፒ

6.2.          ቴክኒካል እና አንድ ኦርጅናል እና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በተለያዩ ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.3.          ለሎት 1 ቢሮ በሚያቀርበው ዝርዝር /ናሙና/ መሠረት ማቅረብ የሚችል

7.     ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሰኞ ዓርብ 230-11 ሰዓት ድረስ የግዥ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 803 በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8.     ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ 11ኛው ቀን ማለትም የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጐ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9.      ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት /ማቅረብ/ አይቻልም።

10. ቢሮው ብዛቱን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ በገለፅነው መሠረት መቀነስና መጨመር የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።

11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011 8 12 61 79/ 011 1 70 30 24/ በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ንግድ ቢሮ ውቤ በረሃ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ

Save Tender