ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አ.ማ. ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ ዎርከ ሾፕ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ባሌስትራዎች፣ የተቃጠሉ ዘይቶችን፣ ሻክል፣ ፕሬዥር ፕሌቶች፣ ካቦዎች የብረት ታንከሮች እና ሌሎች እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር [Gada/NCB/07/2018]
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አ.ማ. ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ ዎርከ ሾፕ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ባሌስትራዎች፣ የተቃጠሉ ዘይቶችን፣ ሻክል፣ ፕሬዥር ፕሌቶች፣ ካቦዎች የብረት ታንከሮች እና ሌሎች እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ወይም ያላት እና በማንኛውም ንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ወይም የተሰማራች፡፡
2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡00 ሰዓት በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም ወይም በመፈረም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሰጥ 15% ቫት ያካተተ መሆን አለበት፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበትን ዋጋ 2% በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ላይ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተወዳዳሪውች የገዙትን ሰነድ እና ደረሰኝ በመያዝ እቃዎችን ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡
7. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት አጠቃላይ ያሸነፉበትን እቃ ሙሉ በሙሉ በመክፈል እቃውን ከጊቢ ማውጣት አለባቸው፡፡
8. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሸያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡
9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
10. ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ ሞጆ ይገኛሉ፡፡
11. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሑድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሰንጋ ተራ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ ህንጻ 7ኛ ፎቅ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-558-25-19
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አክሲዮን ማኅበር
