በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ለ2018 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር- ESLSE/P&T/REQ/2026/02255
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ለ2018 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
· ሎት ሰባት: የተለያዩ የደንብ አልባሳት
· ሎት ስምንት: የተለያዩ የቧንቧ እና የኤሌክትሪክ እቃዎች
· ሎት ዘጠኝ: የተለያዩ ማሽኖች
በዚህም መሰረት፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልገሎት ድህረ ገፅ (web site) ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን የሚያሳይ (supplier list) የምስክር ወረቀት፡፡
3. በሎት ሰባት ላይ ለተጠቀሱት የደንብ አልባሳት ናሙና በቅ/ጽ/ቤቱ ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ ስልጣን ካለው አካል የተሰጠ ማስረጃ (Valid tax clearance)።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ የሚመልሰው በድርጅቱ ድህረ- ገጽ (www.eslse.et) ላይ በERP SYSTEM በዋና መ/ቤት ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ብቻ (ከዚህ ቀደም ያልተመዘገቡ ከሆነ) በሚሰጣቸው መለያ ቁጥር መሰረት የሚሞሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
6. የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ቀን እና ሰዓት ይሆናል።
7. የጨረታ ማስያዣ ለእያንዳንዱ ሎቶች ሲ.ፒ.ኦ 50,000 ብር (ከንግድ ባንክ፤ ከህብረት ባንክ እና ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ብቻ) ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማዕከሉ የሚገባ ይሆናል።
8. ለሁሉም ሎቶች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በቅ/ጽ/ቤቱ ሲፒኦ መቅረብ ግዴታ ነው።
9. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0221162194 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል
