የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ//009/2018 ዓ.ም
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ//009/2018 ዓ.ም
· ሎት -1 ለግቢ ማስዋቢያ የሚያገለግሉ ዕፅዋት /አትክልቶች/ እና ተዛማች ዕቃዎች እንዲሁም ለጥበቃና ለህንፃ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎች ግዥ
· ሎት -2 የሠራተኞች የተለያዩ የደንብ ልብስ ስፌት የአገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላችሁ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድህረ ገፅ ላይ የተመዘገቡ እንዲሁም ማስረጃውን ኮፒና ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ፤ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01፡ ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ላይ 4ተኛ ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን እያንዳንዱን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ዋስትን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው የሚከፈተው መጋቢት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 901 ይከፈታል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት ህንፃ
ስልክ ቁጥር:- 0936 99 35 20/ 0911 36 97 83
በቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
