በደ/ምዕ/አ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1፡- የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፣ ሎት2፡- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ፣ ሎት 3፡- የመስክና የላፕቶፕ ቦርሳ ግዥ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/አ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1፡- የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፣ ሎት2፡- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ፣ ሎት 3፡- የመስክና የላፕቶፕ ቦርሳ ግዥ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች በሚጠይቀው ዘርፍ የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ያላቸው
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፤
4. የአቅራቢነት የምስከክር ወረቀት ያላቸዉ፣
5. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና
ሎት 1፡- የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
ሎት2፡- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
ሎት 3፡- የመስክና የላፕቶፕ ቦርሳ ግዥ ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምርያ በማለት ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ስለጨረታዉ ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያዉ የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ በደንብ በፖሰታ በማሸግ መቅረብ አለበት፡፡
8. ተጫራች በእያንዳንዱ በትክክል ታሽጎ ማህተም በመምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናልና እና ኮፒ የሚል ጽሁፍ በግልፅ መስፈር አለበት፡፡
9. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣው በ15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ሚዛን አማን
