Tender Detail

Tender Details

  • Company TIRUNESH BEIJING HOSPITAL (የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ወይም ልዩ ስሙ ጥምቀተ ባህር ወይም አቃቂ መሿለኪያ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0924777840
  • Website
  • Deadline27 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-03-27 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Health Related Services , Electronics Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የተለያዩ ሎቶችን የሚሆኑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ቁጥር 08/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የተለያዩ ሎቶችን የሚሆኑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

1. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከገቢዎች በጨረታ እንዲሳተፉ የተገለፀበት ደብዳቤ ያላቸው እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ እና በዘርፉ የተሰማሩ የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ሰነድ በነፃ ለሚወስዱ ማህበራት በዘርፋ ስለመደራጀታቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩ የእቃ ወይም አገልግሎት አይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይየስራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅቱ ስም ከድርጅቱ አካውንት ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ሎት 1፡- የሰው መደሀኒትና የህክምና መርጃ መሳሪያ (ስድስት ወር) የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺ ብር)

ሎት 2፡- የላብራቶሪ ሪኤጀንት (ስድስት ወር) የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሎት 3፡- የህክምና ዕቃዎች የጨረታ ዋስትና ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር)

ሎት 4፡- የአንቡላንስ መኪኖች ጥገና ዕቃን ጨምሮ የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሎት 5 ፡- የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች (የኔትወርክ ዕቃዎችና ሴኪዊሪቲና ቪዲዮ ካሜራ)ግዥ የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)

ሎት 6 ፡- የፅዳት አገልግሎት የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺብር/ ዓመታዊ ውል ሎት 7፡-የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገጃ ትሪትመንት ፕላንት ማሽን ከነሥራው ከነኘሮጀክት ግዥ የጨረታ ዋስትና ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/

ሎት 8- የፈርኒቸር እና ላተራል ግዥ የጨረታ ዋስትና ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ለጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ተብሎ በማዘጋጀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቶች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ብቻ በመሙላት የድርጅታቸውን ማኅተምና ፊርማ እኑረው ፋይናንሻል ኮፒ ፣ ቴክኒካል ኮፒ) ፣ ፋይናንሺያል ኦርጅናል 1 እና ቴከኒካል ኦርጅናል 1 በድምሩ 4 ፖስታ በማድረግ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት አያግደውም፡፡ ክኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንዲሁም ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

7. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች ያለምንም አቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ከምችት ያለውና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያነት አስይዞ ተገቢውን ውል በመፈጸም እቃዎቹን በሆስፒታሉ ግቢ ንብረት ከፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

8. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ወይም ልዩ ስሙ ጥምቀተ ባህር ወይም አቃቂ መሿለኪያ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ ስልክ፡- 0934202236 በስራ ሰዓት ብቻ መደወል ይችላል ፡፡

የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል

Save Tender