በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) እንዲሁም ኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኝ የፋብሪካ ማሽነሪና ምርቶችን በግልፅ
የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 45/2018
በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) እንዲሁም ኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኝ የፋብሪካ ማሽነሪና ምርቶችን በግልፅ ባሉበት ሁኔታ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ መጋቢት 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይየሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን።
በመሆኑም
1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ መጋቢት 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALIY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነዱ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት |
የእቃ ግልፅ |
እስከ 22/07/2018 |
23/07/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል |
6. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡ አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
7. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
9. ከላይ በተ/ቁ 8. በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ፡- 011-470-85-03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
