Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ////////////16/2018

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት ከዚህ በታች ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ድረስ ያሉትን እቃዎች ግዥ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች

ማለትም፡-

ሎት 1. የአደጋ መከላከያና ደንብ ልብስ፣

ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች፣

ሎት 3. የተለያዩ ተሽከርካሪ ጐማዎች፣

ሎት 4. የአይቲ እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣

ሎት 5. የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች ዕቃዎች፣

ሎት 6. የህትመት ውጤቶች፣ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።ስለሆነም፡-

1.       በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል በኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት C.R.D.A አጠገብ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

2.       ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት2 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት3 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 4 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት5 10,000 /አስር ሺህ ብር እና ለሎት6 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት 90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantees) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3.       ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 በግዥ ዳይሬክቶሬት ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

4.       ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት ከሲ.አር.. አጠገብ

ስልክ ቁጥር 011 462 1457/ 09 20 27 66 48

የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት

Save Tender