የማራኪ ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ/ም በጀት ለማራኪ ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚሰጥ የተለያዩ 1. የፅዳት፣ 2. አላቂ የቢሮ እቃ እና 3. ፕሪንተር አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የማራኪ ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ/ም በጀት ለማራኪ ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚሰጥ የተለያዩ 1. የፅዳት፣ 2. አላቂ የቢሮ እቃ እና 3. ፕሪንተር አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ማወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
2. ተወዳዳሪዎች እስከ 2018 ዓ.ም. ማጠናቀቂያ ድረስ ባከናወናቸው ተግባራት የመልካም ስራ ውጤት ማቅረብ የሚችል
3. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ሌሎች የሚመለከታቸው ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች 1% ሲፒአ በባንክ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 ብር ማራኪ ጤና ጣቢያ፡፡ ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በማቅረብ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን እቃ ኣይነት አሸናፊው ከተረጋገጠ በኋላ ለ5 የስራ ቀናት ሁሉም ተረጋግጦ ከ5 ተከታታይ ቀናት ውል መውሰድ የሚችል፡፡
7. ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ኦጅናል ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን በ15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት አለባችሁ፡፡
8. ተጫራቾች ማስታወቂያው የአየር ላደ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ማህተምና ቀን ሙሉ ስማቸውና አድራሻ በመግለፅ በቀን 18/7/2018 እስከ / 2/8/2018 ዓ.ም ማስገባት የሚችሉ።
9. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማ/ጤ/ጣ/ግ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በቀን 05/08/2018 ዓ.ም በተዘጋጀው ሳጥን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. መ/ቤቱ ስለጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ከላይ በተገለፀው መስፈርት መሰረት ማንኛውም አቅራቢ መወዳደር ይችላል።
የማራኪ ጤና ጣቢያ
