የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለክልሉ ጤና ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለክልሉ ጤና ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
· ሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ
· ሎት 2 የተለያዩ የህትመት ስራዎችን
· ሎት 3 የሰራተኛ ደንብ ልብስ
· ሎት 4 የመስክ ስራ ተሸከርካሪ ኪራይ /መኪና ኪራይ/
· ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
· በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
· የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
· የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
· የግብር ከፋይ መለያ ምስክር ወረቀት /TIN Number/ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
· የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል መሆን ይኖርባቸዋል።
በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት መግዥያ የማይመለስ ብር 500 / አምስት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ቀርበው በመክፈል ዘወትር በመንግስት ሥራ ሰዓት ለ15 /አስራ አምስት/ ቀናት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
v ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ / የባንክ ዋስትና/
ለእያንዳንዱ ሎት ፡-
Ø ለሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ 100,000 / አንድ መቶ ሺህ ብር / ብቻ
Ø ለሎት 2 የተለያዩ የህትመት ስራዎችን 100,000 / አንድ መቶ ሺህ ብር / ብቻ
Ø ለሎት 3 የሰራተኛ ደንብ ልብስ 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር / ብቻ
Ø ለሎት 4 የመስክ ስራ ተሸከርካሪ /መኪና ኪራይ/ 350,000 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ
Ø ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ / 200,000 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / ብቻ
v በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
v ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሠነዱ ላይ በመጻፍ በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ የመንግስት የሥራ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
v ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ 1 /አንድ/ ኦሪጂናል እና 2 /ሁለት/ ኮፒ ፖስታዎች ለየብቻቸው በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
v ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ አድራሻ፣ ማዕተምና ፊርማቸውን መሙላት ይኖርባቸዋል።
v የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
v አሸናፊው ድርጅት በተወዳደረበት ቦታ ንብረቱን የማቅረብ ግዴታ አለበት።
v ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መ/ቤቱ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
v የጨረታውን ሂደት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት ሂደቱን አያስተጓጉልም።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 473450879 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
ታርጫ
