Tender Detail

Tender Details


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በኢቶል (ETOL) በተመደበ በጀት ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ዴስክቶፕና ላፕቶፕ ከምፒዩተሮች፣ ኤል.ሲ.ዲ ፕሮጀክተር፣ ፕሪንተር፣ መልቲ ፋንክሽን ፎቶኮፒ ማሽን፣ ሄድፎን፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ሸልፎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን እንዲሁም በዩኒሴፍ /UNICEF/ በተመደበ ገንዘብ ደግሞ ለልጃገረድ ተማሪዎች የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EB/EMAS/013/2018

 

የአማራ ብሔራዊ ልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በኢቶል (ETOL) በተመደበ በጀት ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ዴስክቶፕና ላፕቶፕ ከምፒዩተሮች፣ ኤል.. ፕሮጀተር፣ ፕሪንተር፣ መልቲ ፋንክሽን ፎቶኮፒ ማሽን፣ ሄድፎን፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ሸልፎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን እንዲሁም በዩኒሴፍ /UNICEF/ በተመደበ ገንዘብ ደግሞ ለልጃገረድ ተማሪዎች የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1.     የዘመኑ የታደሰ ህጋዊና በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣

3.     የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4.     ዕቃዎች አይነትና ኒካል የፍላጎት ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቸላሉ።

5.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 600.00 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 15 ማግኘት ይችላሉ።

6.     ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (..) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7.     የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 9 ባሉ ንዑሳ ቁጥሮች ላይ በዝርዝር በተቀመጠው መሠረት ይሆናል።

8.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሐሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ግብዓት ጥናትና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 16ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ ማስገባት የሚቻለው እስከ ከጠዋቱ 400 ድረስ ብቻ ይሆናል።

9.     ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ 16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሑድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 400 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 430 ሰዓት ይከፈታል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205654 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

Save Tender