በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከታች የቀረቡትን የምርት ማሸጊያ እቃዎች በጥራትና በብቃት አምርቶ ለማቅረብ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኬኢኮስመኬፋ 007/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከታች የቀረቡትን የምርት ማሸጊያ እቃዎች በጥራትና በብቃት አምርቶ ለማቅረብ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡-
· ብዛት 50,000 የሆነ የሀይድሮጂንፔር ኦክሳይድ ምርት ማሸጊያ ጀሪካን ባለ 25 ሊትር HDPE Jerrycan in capacity & 1.65 kg concentrated 50% by w/w.
· ብዛቱ 46,652 የሆነ የሰልፈሪክ አሲድ ምርት ማሸጊያ ጀሪካን ሊትር High density polyethylene (HDPE) jerrycan in capacity & 1.75 kg Concentrated 98.5% by w/w.
ስለሆነም፡-
1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ/2018 ዓ.ም/ ግብር የከፈሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝርና እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ጨረታውን መሣተፍ ይችላሉ፣
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት እና ከአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ከግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ መግዛት ይችላሉ፤
3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፣
4. ተጫራቾች የእያንዳንዱን አይነት የጀሪካን ሁለት ሁለት ናሙና የማይመለስ ከቴክኒካል ኦፈርና ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ፣ ከዚህ በተጨማሪ ፋይናንሻል ኦፈር ለብቻ በአንድ ፖስታ ታሽገው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዶቹን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ሐሙስ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ቴክኒካል ኦፈሩ ብቻ በዕለቱ ሐሙስ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ የሽያጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ይከፈታል።
6. ጀሪካኖች ተፈትሾ ቴክኒካል ምዘና ያለፉት ብቻ ፋይናንሻል ኦፈራቸው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግድም።
7. አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡- ስልክ ቁጥር 011 554 57 71 /0920935336
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ
