የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት ለመምሪያውና ለተለያዩ የሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት ዕቃዎች፣ የጽሕፈት ዕቃዎች፣ የግንባታ እቃ፣ የጽሕፈት ትርጉም አገልግሎት የደንብ አልባሳት፣ የህትመት ውጤቶች፣ የመኪና ዕጥበትና ግሪስ፣ የመኪና ጎማ ዊል ቫላንስ እና ቋሚ ዕቃዎች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር YS/C/d NCB003/2018 ዓ.ም
የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት ለመምሪያውና ለተለያዩ የሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት ዕቃዎች፣ የጽሕፈት ዕቃዎች፣ የግንባታ እቃ፣ የጽሕፈት ትርጉም አገልግሎት የደንብ አልባሳት፣ የህትመት ውጤቶች፣ የመኪና ዕጥበትና ግሪስ፣ የመኪና ጎማ ዊል ቫላንስ እና ቋሚ ዕቃዎች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም በማስፈለጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
|
ሎት |
የሚገዙ ዕቃዎች የሎት ዝርዝር |
በሲ.ፒ.ኦ የሚያዝ የገንዘብ መጠን |
|
ሎት 1. |
የፅዳት ዕቃዎች |
1,000.00 |
|
ሎት 2. |
የጽሕፈት ዕቃዎች |
1,000.00 |
|
ሎት 3. |
የደንብ አልባሳት |
1,000.00 |
|
ሎት 4. |
የሕትመት ውጤቶች |
1,000.00 |
|
ሎት 5. |
የመኪና ጎማ ዊልቫላንስ |
1,000.00 |
|
ሎት 6. |
የመኪና እጥበትና ግሪስ |
1,000.00 |
|
ሎት 7. |
የጽሕፈት ትርጉም አገልግሎት |
1,000.00 |
|
ሎት 8. |
የግንባታ ዕቃዎች |
2,000.00 |
|
ሎት 9. |
ቋሚ ዕቃዎች |
2,000.00 |
1. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው
2. የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4. የመንግሥት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ላይ ተቀባይነት የለውም--
6. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስም በተዘጋጀው በባንክ በተመሰከረለት የባንክ (C.P.O) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት 60 ቀን ነው።
8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት መቅረብ ይኖርበታል። ተጫራቾች ሾላ ገበያ በሚገኘው በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የማይመለስ 300.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እንዲሁም በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ቢሮ ቁጥር 505 ይከፈታል።
11. የጨረታው መክፈቻ ከስራ ቀናት ውጪና የክብረ በአል ቀናት ከዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሲሆን ይከፈታል፡፡
12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ካላንደር ወይም ስራ የማይኖርበት ከሆነ በቀጣዩ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
13. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር 0116676482
የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ
