Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Athletics federation (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን)
  • Address ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116-47-97-94
  • Websitehttps://eaf.org.et/
  • Deadline14 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-04-14 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 28/2018 የ2018 በጀት ዓመት አመታዊ የደንብ ልብስ በሀገር ውስጥ ጨረታ በግልጽ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 28/2018 2018 በጀት ዓመት አመታዊ የደንብ ልብስ በሀገር ውስጥ ጨረታ በግልጽ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሠረት፡-

1.     በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

2.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው

3.     ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ

4.     ተጫራቾች የመጫረቻ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በታሽገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል

5.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 430 ሰዓት በፌዴሬሽነ ቢሮ ቁጥር5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል

6.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የደንብ ልብስ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል

7.     ተጫራቾች የጨረታ ሣጥን ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩባቸው የደንብ ልብሶች ናሙና ከቢሮ መውሰድ ይኖርባቸዋል

8.     አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

9.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

አድራሻ- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ- 0911142100/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

ፋክስ፡- 0116-45-08-79

ፖ.ሳ.ቁ፡- 13336

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

 

Save Tender