ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ላሉት ቋሚ ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውል ሎት1፡- የሰራተኞች ደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ ኮት እና ሱሪ) እና ሎት2፡- የመታወቂያ ማንጠልጠያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/25/18
ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ላሉት ቋሚ ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውል
· ሎት1፡- የሰራተኞች ደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ ኮት እና ሱሪ)
· ሎት2፡- የመታወቂያ ማንጠልጠያ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የቲን ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-11፡00) እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሠዓት ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክበተረጋገጠ ሰ.ፒ.አ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
