Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ወሎ ዞን የመካነሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅራቢ, አገልግሎት እና የላውንደሪ እጥበት ስራን አውት ሶርስ በማድረግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ቆይታ ማሰራት ይፈልጋል።


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ወሎ ዞን የመካነሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል የተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅራቢ, አገልግሎት እና የላውንደሪ እጥበት ስራን አውት ሶርስ በማድረግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ቆይታ ማሰራት ይፈልጋል፤

ለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1.     በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርቡ

2.     በጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ የተደራጀ ማህበር ካለ በመመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል

3.     የቫት ተመዝጋቢ የሆነ /ነች

4.     የንግድ ፈቃዱ ካፌና ሪስቶራንት ሆቴል፤ ምግብ ቤትና ባርና ሪስቶራንት እና ተመሳሳይ የሆነ ስራ ሊሰራ የሚችል

5.     ጨረታው የሚከናወነው በሎት ነው፡፡

ሎት 1. የተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅራቢ አገልግሎት (ለሶስተኛ ጊዜ)

ሎት 2. የላውንደሪ እጥበት ስራን አውት ሶርስ አገልግሎት

6.     በላውንደሪ ስራ ላይ የሰራተኛ ብዛት 6 የሚሆን እና ቅዳሜ፣ እሁድ የህዝብ በአላትና የአዘቦት ቀን 24 ሰአት ውስጥ ላውንደሪ እጥበት ስራ ላይ በተሟላ ሁኔታ ላይ በመገኘት ማጠብ አለባቸው።

7.     አሸናፊው ተጫራች (ማህበሩ) ላውንደሪ እጥበት ስራ በእንዝላልነት በግዴለሽነት ምክንያት ለሚጠፋ ንብረቶች የመንግስትን ሀብትና ንብረት የሚከፈልና በህግ የሚጠየቅ መሆኑን።

8.     በሆስፒታሉ ህግና ደንብ መሰረት ተገዥ የሆነና ሌሎች ከላውንደሪ እጥበት : ስራ : ጋር የተያያዙ ስራዎችንና የሚሰጠውን ማንኛውንም ተግባር ተቀብሎ መፈፀም የሚችል።

9.     አሸናፊው ድርጅት ማህበሩ/ በሚያሰራው የላውንደሪ እጥበት ስራ ሰራተኛ የሚፈጠር · ማንኛውንም ችግር ተጠያቂ ይሆናል፡፡ በወር የአገልግሎት ክፍያ፣ ደመወዝና በአመት ሁለት ጊዜ ለደንብ ልብስ ግዥ ጨምሮ የላውንደሪ ማጠቢያ እቃዎች ግዥ መጠየቂያ ደመወዝ ጭምር ሊከፍለው የሚችለውን የገንዘብ መጠን ጥቅል ድምር በተዘጋጀው የመወዳደሪያ ሰነድ መሙላት አለበት።

10. የተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከመ/// ሆስፒታል ዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይቻላል፡፡ በጥቃቅን የተደራጁ በነፃ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት 2% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ (CPO) /ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

11. ማንኛውም ተጫራች በተዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በደንብ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ዘወትር በስራ ሰዓት ///አስ//የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ይዘጋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 830 ይከፈታል፡፡ 16 ተኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በአላት ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው መክፈት ይቻላል፡፡ ማንኛውንም የላውንደሪ እጥበት ስራ እቃቸው፡- ለምሳሌ በረኪና ኦሞ፣ ላርጎ፣ ሳሙና እና የእጅ ጓንት ለስራው የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች በራሱ ወጭ አሟልቶ ማጠብ የሚችል የላውንደሪ ስራ ላይ የስራ ክፍሎች የሚገኙበትን አንሶላ፣ ብርድልብስ፣ ትራስ ልብስ ኦአር ላይ ያሉ የተለያዩ ልብሶች የባለሙያ ጋዎን ሌሎችም መታጠብ የሚያስፈልጋቸው ልብሶችን በበረኪና 19 (አንድ ለዘጠኝ ውህድ) በመጠቀም ማቴሪያል በአሸናፊ ድርጅቱ የሚሸፈን ሆኖ በእጅ ማጠብ የሚችል መሆን አለበት።

12. የግብአት አገልግሎት ቢያንስ ለሶስት ወር በቂ የሚሆን በመጋዘን ማስቀመጥ የሚችል

13. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በጨረታውን መሳተፋ የሚፈልጉ መረጃ ከፈለጉ ///ሆስፒታል ከግ///አስ//የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0934 37 02 54 / 0914 34 43 06 / 0923 74 70 44/ ወይም በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

 

መካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

Save Tender