Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት አላቂ ዕቃዎችን ፣ ቋሚ ዕቃዎችን እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ/የጨረታ ቁጥር 05/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት 2018 በጀት ዓመት አላቂ ዕቃዎችን ቋሚ ዕቃዎችን እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1.     ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች

2.     ሎት 2 ህትመት አገልግሎት

3.     ሎት 3 ሌሎች አላቂ እቃዎች

4.     ሎት 4 የውሃ መስተንግዶ አገልግሎት

5.     ሎት 5 የጽዳት እቃዎች

6.     ሎት 6 የደንብ ልብስ

7.     ሎት 7 የኤሌክትሮኒክስ እቃ

8.     ሎት 8 የመኪኖች ማስዋቢያ

መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

1.     ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ

2.     የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣

3.     የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣

4.     ከገቢዎች የተጻፈ የአቅራቢነነት ደብዳቤ ያላቸው፣

5.     የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /Tin No/ ያላቸው፣

6.     በመንግስት ግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድር-ገጽ (WWW.PPA.gov.et)

7.     ተጫራቾች የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ /CPO

. ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች-- 5,000 ብር

. ሎት 2 የህትመት ስራዎች-- 3,000 ብር

. ሎት 3. ሌሎች አላቂ እቃዎች-- 5,000 ብር

. ሎት 4. የውሃ መስተንግዶ አገልግሎት--2,000 ብር

. ሎት 5 የጽዳት እቃዎች--5,000 ብር

. ሎት 6 የደንብ ልብስ--5,000 ብር

ሎት 7 የኤሌክሮኒክስ እቃዎች--20,000 ብር

. ሎት 8 የመኪኖች ማስዎቢያ--5,000 ብር

8.     ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን CPO ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣

9.     ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሚወዳደርበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለበት፣ እስፔስፍኬሽን ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ በተረጋጋ መንገድ ሞልተው ያስገቡ፡፡

10. ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 15 ፎቅ የፋይናንስ ዳይሮክቶሬት በመቅረብና የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ

11. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣

12. /ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣

13. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሽል ኦርጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒው ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል /ለየብቻ/ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ የተወዳደራችሁበትን የሎት አይነት በፖስታው ላይ እየጻፋችሁ አስገቡ ካልጻፋችሁበት ደግሞ ፖስታችሁ እንደማይከፈት እያወቃችሁ የተባሉትን በሙሉ በማድረግ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወደ ህንጻው ስትገቡ በቀኝ በኩል ባለው ሊፍት 15 ፎቅ ፊት ለፊት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፣

14. ጥቃቅንና አንስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰንዱን በነፃ ለመውሰድ

. ካደራጃችሁ /ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፣

. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ፣

15. ተጫራቾች /ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፣

16. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፣ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ 8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፣

17. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 300 ሰዓት ታሽጎ 330 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።

 

ማሳሰቢያ፡-

1.     ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን /ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል።

2.     /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ክፍለ ከተማ፡ አራዳ ወረዳ፣ 1 ፒያሳ/ እስታቲክስ ጎን ዋስትና ንግድ ማእከል እናት ህንጻ ፊት ለፊት 15 ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-127-68-25 ይደውሉ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን

Save Tender