የአራዳ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በ4ኛ ዙር ግዥ ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. የተለያዩ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት 3. የአይት ዕቃዎች፣ 4. የመኪና ኪራይ፣ ሎት 5. የዴኬር ዕቃዎች፣ ሎት6 ሞንታርቦ ከነሙሉ አክሰሰሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 4/2018
የአራዳ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 4ኛ ዙር ግዥ ለማካሄድ የወጣ
ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. የተለያዩ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት 3. የአይት ዕቃዎች፣ 4. የመኪና ኪራይ፣ ሎት 5. የዴኬር ዕቃዎች፣ ሎት6 ሞንታርቦ ከነሙሉ አክሰሰሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማቅረብ የሚገባቸው፡-
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የአቅራቢነት ሰርተፈኬት በዘርፉ ሕጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነትና የግብር መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፤
4. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለሥልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 200 ብር በመክፈል የመንግሥት ግዥ ቢሮ ቁጥር 6ኛ ፎቅ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የመንግሥት ግዥ ቢሮ ቁጥር 6ኛ ፎቅ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላል፡፡
7. ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ስድስተኛው /6ኛ/ ፎቅ በሚገኘው የመንግሥት ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
9. በራሱ ሰነድ ሞልቶ የሚያመጣ ከሆነ ከጨረታው ውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
10. ዕቃዎቹ በቀረበው ናሙና መሠረት የጨረታ አሸናፊ የሆነ ማቅረብ የሚችል ፡፡
11. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በእያንዳንዱ ሎት መሠረት ማስያዝ ይኖርበታል።
12. ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በግልፅ ተጽፎ ሁለቱንም ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. ተጫራቾች ያሸነፈው ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል፡፡
14. የጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት የድጋፍ ደብዳቤ ተቀባይነት የሚኖረው ራሱ በአመረተው ምርት ብቻ ሲሆን፡፡
15. እያንዳንዱ ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በባንክ የተረጋገጠ 5,000.00 (አምስት ሺ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
16. በሚያስገቡት ፓስታ ላይ እያንዳንዱ ሎቱን ጠቅሶ ማስገባት አለበት፡፡
17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አራት ኪሎ በሚገኘው አራዳ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰ/ሀ/ልማት ጽ/ቤት ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ
የአራዳ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት
