የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ በጨረታ መለያ ቁጥር አድ/መ/004/2018ዓ.ም ለ2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉት የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የሆነ ህትመት ስራዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች፣ ሳኒተሪ እቃዎች እና የውሃ የመለዋወጫ እቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር አ/ድ/መ/004/2018 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ በጨረታ መለያ ቁጥር አድ/መ/004/2018ዓ.ም ለ2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉት የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የሆነ ህትመት ስራዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች፣ ሳኒተሪ እቃዎች እና የውሃ የመለዋወጫ እቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እየጋበዝን የእቃዎቹ ዝርዝር ከታች ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል፡፡
|
ምድብ ቁጥር |
የሚገዙ ዕቃዎች አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ብር |
|
ሎት 1 |
የህትመት ስራ ግዥ |
10,000 |
|
ሎት 2 |
ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ |
20,000 |
|
ሎት 3 |
የግንባታ እቃዎች ሳኒተሪ እቃዎች እና የውሃ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ |
50,000 |
|
ሎት 4 |
የኦዲዮ ቪዥዋል እቃዎች |
30,000 |
|
ሎት 5 |
የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች |
30,000 |
|
ሎት 6 |
EV charger (ኤልክትሪክ መኪና ቻርጀር ዕቃዎች) |
15,000 |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
4. አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) በአድዋ ድል መታሰቢያ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000613546867 በመክፈል ደረሰኝ /ስሊፕ/ ይዞ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሽል ኦርጅናልና ኮፒ እና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ በየሎቱ ለብቻቸው ፖስታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ L2 መሰብሰቢያ ክፍል ቢሮ ቁጥር 214 ይከፈታል።
8. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ከ2 ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ለማይቀርብባቸው የእቃ አይነት በሚቀርበው እስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆኖው የሚገኙበት እቃዎችን በአጠቃላይ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበርያ በማስያዝ የግዥ ውል ስምምነት መፈራረም ይኖርባቸዋል።
10. አሸናፊ ድርጅት የሚቀርቡትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
11. የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል።
12. መስሪያቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ፒያሳ አራዳ ህንጻ ፊት ለፊት የአድዋ ድል መታሰቢያ ፋይናንስና አስተዳደር ዳይሬክተር
የአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ
ስልክ ቁጥር ስልክ ቁጥር +251-987929292 +251-986929292 +2519-22-93-13-62
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ
