የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የደንብ ልብስ ጨረታ
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በመስኩ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ስለሚገዛው የሥራ ልብስ በቀረበው ስፔስፍኬሽን መሠረት ልብሱ የተሠራበትን ጨርቅ የተመረተበትን ፋብሪካ፣ የተሠራበት የጥጥና የሴንቲቲክ መጠን ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን ዓይነት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ በሚያቀርቡት ናሙና ላይ ሞዴሉ ወይም የጨርቁን ዓይነት የሚገልጽ በጨረታ ሰነዱ ላይ ካለው ጋር ማገናዘብ በሚችል መልኩ በዕቃዎቹ ላይ ጽፎ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨርቅ ናሙና ከ5 ሳንቲ ሜትር ያላነሰ መሆን አለበት፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት ከዱራሜ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን 15ኛው ቀን 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡00 ሰአት ይታሸግና 3፡15 ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል ሆኖም የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታ ሰነዱን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በሰም የታሸገ ፖስታ ሆኖ ፖስታው ላይ የድርጅታቸውን ስም፣ አድራሻና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በመለየት ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዝርዝርመሠረት በትክክል ማስፈር አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
7. አሸናፊውን ተጫራች ለመምረጥ የሚከተሉትን ዘዴዎች መሠረት በማድረግ ተጫራቾች ያቀረቧቸው የጨረታ ሰነዶች ይገመገማሉ፡፡
ሀ. የመወዳደሪያ ዋጋ .... 80%
ለ. የዕቃው ጥራት... 20%
8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት 5(አምስት) ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና (ፐሮፎርማንስ ቦንድ 10% የባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ) በማቅረብ ውል መፈራረም አለበት፡፡
9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ የሚሰጡት ዋጋ የሚጫረቱበትን የዕቃ ዋጋ ብቻ ይሆናል በመሆኑም የማጓጓዣና ሌሎች ማናቸውንም ወጪዎች አያካትትም፡፡
10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ያቀረቡት ዋጋ ቢያንስ ለ6‰ (ስልሣ) ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል።
11. ባለሥልጣኑ መ/ቤት ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 251911973776/+251926545089
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን
