Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Roads Authority (የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን)
  • Address ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-3-722825
  • Websitehttps://aacra.gov.et/
  • Deadline23 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-04-23 00:00:00
  • Categories Packaging And Labelling , Industry And Factory , Products

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገለገሉ ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀቶች

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገለገሉ ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 

.

የዕቃው ዓይነት

ብዛት

የጨረታ መነሻ ነጠላ ዋጋ ቁጥር

የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋ

የጨረታ .ቁጥር

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1.

ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀት

40,000 (በቁጥር)

9.00 (ዘጠኝ ብር)

360,000.00 (ሶስት መቶ ስልሳ ሺህ)

//////

/01-2/2018

30ቀን

ሚያዝያ 15 ቀን 2018 . ሰዓት 8:00

ሚያዝያ 15 ቀን 2018 . ሰዓት 8:30

 

1.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በባለስልጣን /ቤቱ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 በመምጣት ብር 200 በመግዛት በገርጂ ቱቦ ማምረቻ በሚገኘው የባለስልጣን /ቤቱ //ቤት በመሄድ ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ።

2.     የተጠቀሰውን ንብረት ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በኤንቨሎፕ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ቀን ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ሳር ቤት በሚገኝው በባለስልጣን /ቤቱ 3 ፎቅ የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 144 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾቹ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚያስረዳ ህጋዊ ሰነድ የነዋሪነት መታወቂያ ፓስፖርት ወይም ፋይዳ ምዝገባ ማያያዝ አለባቸው።

5.     ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለስልጣን /ቤቱ ቢሮ ቁጥር 144 ይከፈታል።

6.     ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድር ራሳቸውን የሚያገለግሉ ወይም ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው ባለስልጣን /ቤቱ ገቢ ይሆናል።

7.     የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸባቸው 7 የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ ፈል ይኖርባቸዋል።

8.     ለባለስልጣን /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ

ስልክ ቁጥር 011-372-89-47

 

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

 

Save Tender