የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በሥሩ ለሚያስተዳድራቸዉ ሠራተኞች ለ2018 ዓ/ም አገልግሎት የሚሆን ተሰፍተዉ የተዘጋጁ የተለያዩ ደንብ ልብሶችን፣ ብትን ጨርቆችን፣ ጫማዎችንና ሌሎች ዕቃዎችን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘረዘረዉ መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሠራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፣ ኦ.ደ.ዱ.እ.ድ - 09/2018
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በሥሩ ለሚያስተዳድራቸዉ ሠራተኞች ለ2018 ዓ/ም አገልግሎት የሚሆን ተሰፍተዉ የተዘጋጁ የተለያዩ ደንብ ልብሶችን፣ ብትን ጨርቆችን፣ ጫማዎችንና ሌሎች ዕቃዎችን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘረዘረዉ መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታዉ ላይ እንድትሳተፉ ድርጅቱ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸዉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታዉ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመስስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል አዲስ አበባ ከተማ፤ ቀበና አይል ሊቢያ አጠገብ ከሚገኘዉ የድርጅቱ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቶች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም በመታገዝ የደንብ ልብሱን ዝርዝር በማየት እያንዳንዱን ዕቃ ልብስ የሚያቀርብበትን ዋጋ በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ በኦሮሚያ ደንና ዱር እንሰሳት ድርጅት ስም ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በማሠራት ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸዉን በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ ከሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ጧት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ወስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ማንኛዉም ተጫራች አንዱ ተጫራች ባቀረበዉ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
6. ድርጀቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ለተጨማሪ መረጃ ከታች የተገለጸውን ስልክ ቁጥር በመደወል ወይም በጽሑፍ መጠየቅና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፣ አዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር፤
አራዳ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 07፣
ቀበና ኦይል ሊቢያ አጠገብ
ስልክ ቁ.011-122-00-20/011-124-02-58
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
