የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት የተለያዩ መጽሐፍት ሽፋን ህትመት ሥራ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው በህትመት ዘርፍ የተሰማሩ ማተሚያ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት
የተለያዩ መጽሐፍት ሽፋን ህትመት ሥራ አገልግሎት ግዥ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር EMPDE/NCB/19/2018
ድርጅታችን የተለያዩ መጽሐፍት ሽፋን ህትመት ሥራ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው በህትመት ዘርፍ የተሰማሩ ማተሚያ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. በዘርፉ ተዛማጅነት ያለዉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ. ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት መሆኑን።
2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችለሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲ.ፒ. ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
5. ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድርጅቱ አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደዉ መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ታጥፎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ Tel / 011 646-3481 መረጃ ማግኘት ይቻላሉ።
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት
