Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማእከል
  • Address አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ወይንም መድኃኒያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤ ትልቁ አደባባይ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው 100 ሜትር በስተግራ ገባ ብሎ : አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline13 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-05-13 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Sport Materials And Sportswear

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ለ2018 ዓ.ም የስፖርት ትጥቆች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የስፖርት ትጥቅ የወጣ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 03/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል 2018 . የስፖርት ትጥቆች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1.     ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማንነታቸውን የሚገልፅ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

2.     ተጫራቾች በሚወዳደርበት ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ (የአቅራቢ ምዝገባ ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ፤ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።

3.     ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ክፍለ ከተማ፤ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸው መገለፅ አለበት።

4.     በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት።

5.     ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል 1 ፎቅ ላይ ///አስ/ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባቸዋል።

6.     ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በታሸገ ኤንቭሎፕ አርጅናል እና ፎቶ ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል።

7.     ተጫራ ማዕከሉ ባወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ የግብዓቶችን ዋጋ በማስፈር የማቅረብ እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ስም የተሰራ .. 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9.     ጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት 10ኛው የሥራ ቀን 800 ላይ ታሽጎ 830 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል 1 ፎቅ ላይ በግልፅ ይከፈታል።

10. ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው ለሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ናሙና ማስታወቂያ ከወጣበት 10ኛው (ጨረታ በሚከፈትበት) ቀን 430 እስከ 530 ባለው ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተባለው ሰዓት ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ይሰረዛል።

12. ተጫራ ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ያሸንፉበትን ግበአት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡ለሚመለከተው አካልም በደብዳቤ ይገልፃል።

13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ማዕከሉ ንብረት ፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

14. ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ወይንም መድኃኒያለም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት ትልቁ አደባባይ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው 100 ሜትር በስተ ግራ ገባ ብሎ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል

Save Tender