Tender Detail

Tender Details

  • Company በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ
  • Address , Phone: 0115545771
  • Website
  • Deadline08 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-06-08 10:30:00
  • Categories Packaging And Labelling , Plastic Raw Materials And Products

በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ፋብሪካ ከታች የቀረቡትን የምርት ማሸጊያ እቃዎች በጥራትና በብቃት አምርቶ ለማቅረብ ልምድ፣ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ኬኒኮአመኬፋ 006/2018

 

በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ፋብሪካ ከታች የቀረቡትን የምርት ማሸጊያ እቃዎች በጥራትና በብቃት አምርቶ ለማቅረብ ልምድ፣ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

ብዛቱ 83,200 ባለ 50 ኪሎ ግራም የአልሚኒየም ሰልፌት ምርት ማሸጊያ ማዳበሪያ ድርጅቱ በጨረታ ሰነዱ በሚያስቀምጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ከሀገር ውስጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

1.     ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ/2018 ዓ.ም/ ግብር የከፈሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ጨረታውን መሣተፍ ይችላሉ፣

2.     ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤትእና ከአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ከግዥ ከፍስ ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ መግዛት ይችላሉ፣

3.     ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፣

4.     ተጫራቾች ሁለት የማዳበሪያ ናሙና የማይመለስ ከቴክኒካል አፈርና ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ፣ ከዚህ በተጨማሪ ፋይናንሻል አፈር ለብቻ በአንድ ፖስታ ታሽገው አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ የግዥ የስራ ሂደት ቢሮ እስከ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዶቹን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት በ4፡00 ይዘጋል።

5.     ጨረታው ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቴክኒካል ኦፈሩ ብቻ በ4፡30 በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈት አያግድም። ቴክኒካል ምዘና ናሙና ፍተሻ በድርጅቱ በራሱ ይከናወናል።

6.     ማዳበሪያው ተፈትሾ ቴክኒካል ምዘና ያለፉት ተጫራቾች ብቻ ፋይናንሻል ኦፈራቸው ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰአት በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መክፈት አያግድም።

7.     አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብሪሪያ፡- ስልክ 011 554 5771

09 20 93 53 36 ኬኢኮአመፋ 

በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ

መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ

Save Tender