Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
  • Address ሆሳዕና ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910062954
  • Website
  • Deadline16 Jun 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price50.00
  • opening date2026-06-16 14:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት ክልል፣ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በጀታቸውን በወቅቱ ለመያዝ እንዲረዳቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ አይነት የፖሊስ ደንብ ልብስ እና የተለያዩ አይነት የሚሊተሪ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የግዥ ማስታወቂያ ቁጥር //02/2018 . የተያዩ ይነት ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን 2019 በጀት ዓመት ክልል፣ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በጀታቸውን በወቅቱ ለመያዝ እንዲረዳቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ አይነት የፖሊስ ደንብ ልብስ እና የተለያዩ አይነት የሚሊተሪ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች -

1.     ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው፣ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፍኬት ያለው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የትብብር / ማቅረብ የሚችል፣

2.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/Bid Bond/ ለሚያቀርቡት የዕቃውን ከጠቅላላ ዋጋ 2% /CPO/ ወይም ሌተር ኦፍ ሬዲት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3.     ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው የተሞላው ዋጋ ከዘጠና ቀናት (90) በታች መሆን የለበትም።

4.     ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

5.     የቴኒካል ስፔስፍኬሽን እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቅጂ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6.     ተጫራ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል 15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 1100 ሰዓት ድረስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ግዥና ፋይ//አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

7.     ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8.     ጨረታ የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 0600 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 08:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

9.     ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በሚዋዋልበት ጊዜ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 25% የመጨመር አለው፡፡

11. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ሞባይል ቁጥር 0910062954 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ሆሳዕና

Save Tender