Tender Detail

Tender Details

  • Company Berhan International Bank S.C
  • Address , Phone: 011 663 2097
  • Website
  • Deadline22 Jun 2026, 5:58 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-06-07 17:57:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

ብርሃን ባንክ በ2018 በጀት ዓመት ለሰራተኛች አገልግሎት የሚውል ጃኬት ግዥ ለማከናወን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


በድጋሚ የወጣ የጃኬት ግዥ ጨረታ

አገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር ብ/ባ/ግጨ/ደል/2025/26/23

  1. ብርሃን ባንክ በ2018 በጀት ዓመት ለሰራተኛች አገልግሎት የሚውል ጃኬት ግዥ ለማከናወን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) መልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቶች ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት እና የታክስን ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  4. ተጫራቶች የማይመለስ ብር 345.00 (ብር ሦስት መቶ አርባ አምስት) በማንኛውም የብርሃን ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈጽመው ደረሰኙን በማቅረብ ከባንኩ ዋና መ/ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ድልድይ ወመሳድኮ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከሰፕላይ ቼን እና ውል አስተዳደር መምሪያ ቢሮ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን ህጋዊ ሰነዶችና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሰነድ በአንድ ፖስታ እና የዋጋ ሰነድ በሁለተኛ ፖስታ በዋና እና በኮፒ ማቅረብ ሲኖርባቸው ለሚሳተፉበት ጃኬት ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው ፡፡
  6. ተጫራቶች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት በሚገኝው ቦሌ ድልድይ ወመሳኮድ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከሰፕላይ ቼን እና ውል አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለጸው ቢሮ ይከፈታል፡፡
  8. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ብርሃን ባንክ አ.ማ

ከሰፕላይ ቼን እና ውል አስተዳደር መምሪያ

ስልክ ቁጥር0116632097/0116507422

Save Tender