በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለታጠቅ እና ለሙገር ጥበቃ ፅዳት መስተንግዶ የጉልበት እና ለተለያዩ ሥራዎች የሰው ሀይል የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀገር ውስጥ የጨረታ ቁጥር
ሙሲፋ/10/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለታጠቅ እና ለሙገር ጥበቃ ፅዳት መስተንግዶ የጉልበት እና ለተለያዩ ሥራዎች የሰው ሀይል የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018ዓ/ም)፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከተጨማሪ እሴት ታከስ ጋር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት (ገርጂ መንገድ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ህንፃ) ከሚገኘው የግብ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሀገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ሳደ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶከመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጥዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በገዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በገዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ስልክ:- 0114420216
ፋክስ:- 0114420688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
