ፋብሪካችን የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሎትን የብረታ ብረት ተረፈ-ምርቶችን፤ Paint-ing Cane, Carton, Welding Electrode Tips, Old Griding Disks በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ፋብሪካችን የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሎትን የብረታ ብረት ተረፈ-ምርቶችን፤ Paint-ing Cane, Carton, Welding Electrode Tips, Old Griding Disks በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች ግለሰቦች ማስረጃቸውን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኩባንያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ሰኔ15 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡
-ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትሹ ተወዳዳሪዎች አንዱን ኪሎ ግራም የምትገዙበትን ዋጋ በመግለጽ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ ቦሌ መንገድ የአሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ቢትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንጻ 4ኛ ወለል በሚገኘው የኩባንያው ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
-የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ግለሰብ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የራሳቸው ትራንስፖርት በማቅረብ ተረፈ-ብረቶቹን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የገዙትን ጥሬ ዕቃ የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ኩባንያው ሌላ ጨረታ በማውጣት የሚሸጥ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
- ኩባንያው ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልከ ቁጥር፣ 251-5522681/ 251-5522731
የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ኩባንያ