Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ ተሽከርካሪዎች የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት፤ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፤የመገናኛ መሳሪያዎች፣ኮስሞቲክስ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፤ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ነዳጅ፤ ምግብ ነከ ዕቃዎች የቅባት እና የጥራጥሬ እህሎች፤ለውዝ እንዲሁም ሌሎ


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

ቁጥር 37/2018

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ /ቤት በቅ//ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ ተሽከርካሪዎች የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት፤ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፤የመገናኛ መሳሪያዎች፣ኮስሞቲክስ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፤ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ነዳጅ፤ ምግብ ነከ ዕቃዎች የቅባት እና የጥራጥሬ እህሎች፤ለውዝ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋርተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስከርወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

2.
ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ 200- 1200 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 200-600 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ . 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

3.
በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሐራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.. መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩከ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንከ የተረጋገጠ . ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4.
ጨረታው ሚካሄደው በሞያሌ //ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወከሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡

5.
ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም /ጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው::

6.
ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 345 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዘግቶ 400 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡

7.
ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀርየጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡

8.
ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት .. (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ 3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

9.
አሽናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

10.
ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (C.P.O) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

11.
/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464441415/0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡



በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ

ቅርንጫፍ /ቤት

Save Tender