Tender Detail

Tender Details


ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ እቀዎችን የኤሌክትሪክ አቃዎች ባለ 36 እና 18 ዋት፣ የታንቡራታ የእንጨት በር፣ ጅብሰም ቦርድ ቁርጥራጭ፣ የእንግዳ ወንበር፣ የአልሙንየም ቁርጥራጮች፣ ልዩ ልዩ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ መስታዎቶች፣ የሞራሌ ቁርጥራጭ እንጨቶች፣ የዲሽ ሳህኖች እና የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መሸጥ ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ይሓ ሪል እስቴት /የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ እቀዎችን የኤሌክትሪክ አቃዎች ባለ 36 እና 18 ዋት፣ የታንቡራታ የእንጨት በር፣ ጅብሰም ቦርድ ቁርጥራጭ፣ የእንግዳ ወንበር፣ የአልሙንየም ቁርጥራጮች፣ ልዩ ልዩ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ መስታዎቶች፣ የሞራሌ ቁርጥራጭ እንጨቶች፣ የዲሽ ሳህኖች እና የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች በማሟላት መጫረት ይችላሉ።

በዚህም መሰረት ተጫራቾች -

1.     የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብርበመክፈል መግዛት ይችላሉ፣

2.     የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባትተከታታይ የስራ ቀናት ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል 2 ፎቅ መግዛት ይቻላል።

3.     ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብርበይሓ ሪል እስቴት /የተ/የግ/ማህበር ሥም ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይኖርበታል።

4.     ተጫራች በጨረታ ሰነዱ የተያያዙ እቃዎች ኮድ 1 ኮድ 2 ኮድ 3 የእቃዎችን ዝርዝር በማየት ለእያንዳንዳቸው ለየብቻ የሚገዙበት ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።

5.     ተጫራች አሸናፊ መሆኑን በስልክ ከተነገረው እና ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ወደ ድርጅቱ 2 ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ ክፍያውን ከፍሎ እቃዎቹን በተጠቀሱት ቀናት ማንሳት ይኖርበታል።

6.     ተጫራች ጨረታውን አሸናፊ መሆኑን ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ክፍያውን ከፍሎ እቃዎቹን ለማንሳት በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሱት የሥራ ቀናት ውስጥ ለመቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆን ቢቀር ያስያዘው CPO ለይሓ ሪል እስቴት /የተ/የግ/ማህበር ሂሳብ ገቢ ይሆናል።

7.     ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን  8 (ስምንተኛው የሥራ ቀንከጠዋቱ 400 ሰዓት ይሆናል።

8.     ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 8 (ስምንተኛው የሥራ ቀንከጠዋቱ 430 ሰዓት ይሆናል።

9.     ተጫራች የሚያቀርበውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ የታሸገ ሲሆን፣ በኢንቨሎፑ ላይ የተጫራች ማንነት መግለጽ ይኖርበታል።

10.ተጫራች ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ካላሟላ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል።

11.ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላል።

አድራሻ፡አዲስ አበባ ስቴድየም ፊት ለፊት ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ስልክ ቁጥር፡የቢሮ 011 558 0129/011 557 6954

ማሳሰቢያ፡ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

 ይሓ ሪል እስቴት /የተ/የግ/ማህበር

Save Tender