Tender Detail

Tender Details


በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ እቃዎች፣ dorco /ምላጭ/ Mosquito net /አጎበር/፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ በግልፅ እንዲሁም Hair clipper /ቶንዶስ/፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጫማ፣ welding electrod፣ dorco /ምላጭ/ እና Woven bag በሀ


የጨረታ ማስታወቂያ ጥር 31/2018 .

 

በጉምሩ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ /ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ እቃዎች፣ dorco /ምላጭ/ Mosquito net /አጎበር/ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ በግልፅ እንዲሁም Hair clipper /ቶንዶስ/ ኮስሞቲስ፣ ተሽከርካሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጫማ፣ welding electrod dorco /ምላጭ/ እና Woven bag በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-

1)     በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር /ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሽከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም እድሜው -18-አመት በላይ የሆነ የኗሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል

2)     በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር /ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል፡፡

3)     የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊዮን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ ያስፈልገውም

4)     በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡

5)     ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ /ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 0300 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ

6)     ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፈደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ /ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 350 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው

7)     የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ //ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 350 ሰዓት ተዘግቶ 400 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሐራጅ ጨረታው 430 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል፡፡

8)     ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 05 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው: እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡

9)     ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡

10)            ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ //ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት ከሰዓት በኋላ 800 ሰዓት እስከ 1000 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጠዋት 300 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡

11)            ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ የእቃው መነሻ ዋጋ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም የእቃው መነሻ ዋጋ 2 ሚሊዮን ብር በታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

12)            መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደው መጠየቅ ይችላ፡፡

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ /ቤት

Save Tender