የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2010 በጀት አመት በ5 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ (01/001-05/2019)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2010 በጀት አመት በ5 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት 1 |
የተለያዩ የምግብ ግብዓት ግዥ |
100,000.00 СРО |
|
ሎት 2 |
የተዘጋጀ /የበሰለ/ የምግብ አቅርቦት ግዥ |
100,000.00 CPO |
|
ሎት 3 |
የተለያየ ጽዳት እቃዎች |
100,000.00 СРО |
|
ሎት 4 |
የተለያዩ አልባሳት |
50,000,00 СРО |
|
ሎት 5 |
የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ |
50,000,00 СРО |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና የፋይናንስ መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች
በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ መዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 የብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር 100000650559 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከቢሮው ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ብቻ ሞልተው እና አሽገው ኤንቨሎፕ ላይ አርጂናልና ኮፒ ብለው በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን፣ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆን እናሳውቃለን፡፡
8. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፤ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ነው፡፡
ማሳሰቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
አድራሻ፣ አ/አ/ሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ ደጃች ውቤ ከጊዮርጊስ ቤተክሪስቲያን ወደ አፍንጮ በር በሚወስደው መንገድ የስድስት ኪሎ ፈረንሳይ ታክሲ መጫኛ ጋር ህንጻ 1888 ላይ 2ኛ ፎቅ
ስልክ 0942129792/0947951760/10927212765
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
