የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
ዕቃው የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታው መዝጊያ |
የጨረታው መክፈቻ |
ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
|
ሎት 1 |
ያገለገሉ ጎማዎች እና ቋሚ እቃና መለዋወጫዎች |
|
ዋናው መስሪያ ቤት (አዲስ አበባ) |
25/10/2018 |
4:00 |
25/10/2018 |
4:30 |
አአ |
|
ሎት 2 |
የተለያዩ መለዋወጫዎች የመኪና እና ማሽነሪዎች |
|
ቧንቧ ውሃ |
29/10/2018 |
4:00 |
29/10/2018 |
4:30 |
ሻኪሶ |
|
ሎት 3 |
የማሽነሪ መለዋወጫዎች የካት፤ የማሽነሪ እና የመኪናዎች |
|
ቀንጢቻ |
29/10/2018 |
4:00 |
29/10/2018 |
4:30 |
ሻኪሶ |
|
ሎት 4 |
የማሽነሪ እና የመኪና መለዋወጫዎች |
|
ሻኪሶ |
29/10/2018 |
4:00 |
29/10/2018 |
4:30 |
ሻኪሶ |
|
ሎት 5 |
ማሽነሪዎች (የተለያዩ ከባድ ተሸከርካሪ ማሽኖች) |
|
ቀንጢቻ፤ ካአሊን ፋብሪካ መጋዶ፤ ኡላኡሉ |
29/10/2018 |
4:00 |
29/10/2018 |
4:30 |
ሻኪሶ |
|
ሎት 6 |
ቁርጥራጭ ብረቶች (በድጋሚ የወጣ) |
|
ዋናው መስሪያ ቤት ቀንጢቻ፤ሻኪሶ ካኦሊን ፋብሪካ፤ መጋዶ፤ ኡላኡሎ አ.አ እና ድሬዳዋ |
29/10/2018 |
4:00 |
29/10/2018 |
4:30 |
ሻኪሶ |
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች መመሪያዎች፡-
1. የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ብሎክ 2፣ ሻኪሶ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግንባር በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤
2. የጨረታ ሰነዱን የዝዙ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ጨረታውን ለመክፈት 20 ደቂቃ እስኪቀረው ድረስ ዘወትር በስራ ቀናት ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቅርንጫፍ በመገኘት ከኮርፖሬሽኑ በሚወከሉ ሰራተኞች አስጎብኚነት በአካል በመገኘት ባሉበት ሁኔታ መመልከት ይቻላል፡፡
3. ተጫራቾች ለሚገዟቸው ንብረቶች የሰጡትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ከሰነዳቸው ጋር የማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ለሆኑትና ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) በንግድ ባንክ ከሆነ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ይታሰብላቸዋል፡፡ ለተሸነፉት ተመላሽ ይደረጋል፡፡
4. በኪሎ ግራም ለሚሸጡ ንብረቶች ተጫራቹ በሚገዛቸው ጠቅላላ ዋጋ ስሌት መሠረት 20% የጨረታ ማስከበሪያ የማስያዝ ግዴታ አለበት።
5. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በላዩ ላይ ድርጅቶች ከሆኑ ማህተም ያረፈበት፣ ግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ ሶስት ፊርማ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቹ ሲወዳደር መለኪያና ዋጋውን በግልጽ መሙላት ይጠበቅበታል፡፡ ግልጽ መለኪያ እና ዋጋ ያላስቀመጠ ተወዳዳሪ ከጨረታው ይሰረዛል።
8. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንን በተመለከተ ከላይ በሰንጠረዥ ለየቅርንጫፉ እና ዋናው መ/ቤት በተገለጸው ቀን እና ሰዓት መሰረት ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 በየአድራሻቸው ማለትም በዋናው መ/ቤት፣ ሻኪሶ በሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች አይነትና ዋጋ በቁጥርና በፊደል ስርዝ ድልዝ የሌለበት ገልጸው በታሸገው ኤንቨሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ የሚኖርባቸው ሲሆን ገዥ የሚሆነው የነጠላ ዋጋው ይሆናል፡፡
10. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0911622263 ወይም በ0913104872 /ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
11. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. በየሎቱ የቀረቡ እቃዎችን ብዛት ከጨረታ ሰነዱ ላይ የምታገኙ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
+251-0911622263
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ
0913104872
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
