ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር ለምርት ስራ አገልግሎት የሚውል Maize flour (Fine) በሀገር ውስጥ ግለጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማኅበር
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር WVD34/2018-09
1. ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዩን ማህበር ለምርት ስራ አገልግሎት የሚውል Maize flour (Fine) በሀገር ውስጥ ግለጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከአክሲዮን መህበሩ ቅ/ጽቤት አዲስ አበባ ወይንም ከዋናው መስሪያ ቤት ኮምቦልቻ መግዛት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በትክክል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ, በ (C.P.O) ወይንም በባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ኮምቦልቻ ዋናው መ/ቤት ወይም አዲስ አበባ ቅ/ጽ ቤት ፓፓሲኖስ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 143 ወይም 144 እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
3. ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋ በ3ኛው ቀን ኮምቦልቻ (ወሎ) በዋናው መስሪያ ቤት ከጧቱ 4 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
4. ይህ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
5. አ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን መሉበሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
ስልክ ቁጥር - 033-5510627/5510211/0973424242 (ኮምቦልቻ)
ስልክ ቁጥር - 011-5530124/5513797/0970230571 (አዲስ አበባ)
ራስ ደስታ ዳምጠው ጎዳና ፓፓሲኖስ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ
የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር
