Tender Detail

Tender Details


ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቀጥር 01/2019

 

ሆራይዘን አዲስ ጎማ //የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

1.     የከራሸር ሮለሮች

2.     የተለያዩ የብረት ሞልዶች

3.     የብረት ኮንቴነሮች

4.     ልዩ ልዩ ሽቦዎች

5.     ስኮርች ኮምፓወንድ

6.     የብረት፣ የፕላስቲክ እና የእንጨት ፓሌቶች

7.     የተለያየ መጠን ያላቸው ብላደሮች

8.     ያገለገሉ መካኒካል ማሸንስና ስፔርፓርቶች

9.     የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌትሪክ ገመዶች

10.                        አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የጎማ የውስጥ ላስቲኮች (ከመነዳሪ )

11.                        የተጋቡ የብረት በርሜሎች

12.                        የተጋቡ ፕላቲከ በርሜሎች

13.                        በጥሩ ይዞታ ላይ ያሉ ያገለገሉ ዘይቶች

14.                        ብረታ ብረቶች

15.                        እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች

በዚህም መሠረት ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በሙሉ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.     ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡

2.     የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከኩባንያው የምርት ሽያጭ ቢሮ መግዛት እና እቃዎቹን ማየት ይችላሉ፡፡

3.     ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይየእያንዳንዱን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በግልፅ ሞልተው፤ ሙሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን ጽፈው ከፈረሙበት በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓም ከጥዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ሳሪስ በሚገኘው ዋናው በሽያጭ ቢሮ ፊት ለፊት ባለው የጥበቃ በር ቁጥር 2 ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሣጥኑ በዚሁ እለት ከጥዋቱ 405 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ጨረታው ሐምሌ 18 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 420 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡

4.     ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦ ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ

ስልከ ቁጥር 011-442-15-55/234 ወይም 251974024142 መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

 

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ሀ/የተ/የግ/ማህበር

 

 

 

 

 

Save Tender