በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በሀገር ውስጥ ገልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሀገር ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ሙሲፋ/19/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በሀገር ውስጥ ገልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018 ዓ/ም)፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከተጨማሪ እሴት ታከስ ጋር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት (ገርጂ መንገድ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ህንፃ) ከሚገኘው የፋብሪካ የግዥ _ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 120,000.00 (አንድ መቶ ሀያ ሺህ) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንከ ጋራንቲ ከቴክኒከ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም.ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ጨረታው በዕለቱ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም.ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ 0114420216
ፋስክ 4 0114420688
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገርሲሚንቶ ፋብሪካ
አዲስ አበባ
