የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለሚገነባቸው የተለያዩ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ እንዲሁም የግንባታ ብረት ከባ/ዳር፣ ከአዳማ ፣ ከገላን፣ ከሸኖ እና ከቢሾፍቱ ከተሞች ከሚገኙ ፋብሪካዎች ፕሮጀከቶች ወዳሉበት ከተሞች ስሚንቶ እና ብረት ለማጓጓዝ ህጋዊ ከሆኑና ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
የሲሚንቶ እና ብረት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዘመን/ማሽግ/ 01/2019
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለሚገነባቸው የተለያዩ ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ከለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ እንዲሁም የግንባታ ብረት ከባ/ዳር፣ ከአዳማ ፣ ከገላን፣ ከሸኖ እና ከቢሾፍቱ ከተሞች ከሚገኙ ፋብሪካዎች ፕሮጀከቶች ወዳሉበት ከተሞች ስሚንቶ እና ብረት ለማጓጓዝ ህጋዊ ከሆኑና ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ስመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፋቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የባለቤትነት መታወቂያ ሊበሬ ያላቸው
2- የጨረታ ሰነዱን ባዳር ከተማ በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ኮብል አከሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ህንጻ እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘዉ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመገኘት የማይመለስ 500 ብር ከፍሎ መውሰድ ይችላል፡፡
3- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይተናት ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ ባህር ዳር ከተማ በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 በጀት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4- ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ይዘጋና በዚያኑ ቀን 8፡30 ይከፈታል። 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በዚያው ቀን 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል።
5- ዝርዝር የጨረታ መመሪያን እና የውል ይዘቱን እንዲሁም የሚገዙትን አገልግሎቶች ከጨረታ ሰነዱ በዝርዝር የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሞላት አለበት።
6- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
7- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር 058-2180538/0927605599/0918305949/ 0918816732/0939230303
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
