የጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለለኛ ዙር የትራንስፖርት የህትመት እና የኤሌክትሮኒከስ እቃ ጥገናዎችን በአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
የጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለለኛ ዙር የትራንስፖርት የህትመት እና የኤሌክትሮኒከስ እቃ ጥገናዎችን በአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1 ሎት የትራንስፖርት
2 ሎት2 የህትመት እና
3. ሎት3 የኤሌከትሮኒከስ እታ ጥገናዎችን በእገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ እወደድሮ መግዛት
ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት
ይኖርባቸዋል፡-
ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስከ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢነት ሊስት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የሚወዳደሩት በሚያመረቱት እታ ወይም ተጨማሪ እሴት ለጨመሩት እታ ሲሆን ከዚህ ውጭ ለሆኑ እቃዎች የሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና ሲፒኦ (epo) በማስያዝ ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች በሚያመርቱት እቃ ሲወዳደሩ እና ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ሲያመጡ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል::
ተጫራቾች ሎት1 እና ሎት3 አገልግሎቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ
የጨረታ ሰነዱን በጉለሌ ከ/ከተማ ከወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት ሰነዱን በማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል፡፡
ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 3:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ከ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጡት ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም ፡ የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 01/ የትራንስፖርት የሚሆን ብር 10,000 (አሥር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 02/ የህትመት 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ሎት3 የኤሌክትሮኒክስ የሚሆን ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
የህትመት ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳ ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት የአሸነፉበትን ዋጋ መጠን እና ብዛት 25% ተጨማሪ ትዕዛዝ መጠየቅ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
መ/ቤቱ ከውል በፊት እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚችል መታወቅ አለበት፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
አድራሻ፡- ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 011-1-23-43-69 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት
