Tender Detail

Tender Details


የአ/ቃ/ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ለሴክተሮች የሚያስፈልጉ የአገልግሎት ግዥዎች /የህትመት ሥራዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የድንኳን እና ዲኮር አገልግሎቶች እና የዋንጫዎች/ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019 .

 

የአ///ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ለሴክተሮች የሚያስፈልጉ የአገልግሎት ግዥዎች /የህትመት ሥራዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የድንኳን እና ዲኮር አገልግሎቶች እና የዋንጫዎችግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1የህትመት ሥራዎች፤

ሎት 2የመኪና ኪራይ፤

ሎት 3የድንኳን እና ዲኮር አገልግሎቶች፤

ሎት 4 የዋንጫዎች ግዥ፤

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1.     በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ

2.     የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ያለው

3.     የዘመኑን ግብር የከፈሉና በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

4.     ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

5.     የጨረታ ማስከበሪያ CPO

ሎት፡-1- 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ/

ሎት 2- 45,000.00 /አርባ አምስት ሺህ ብር ብቻ/

ሎት 3- 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር ብቻ/

ሎት 4 20,000.00/ሃያ ሺህ ብር ብቻሲፒኦ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት በሚል ያሰራሉ።ተጫራቾች የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻበመክፈል እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ለሚወዳደሩ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ብቻ የተሳተፉ እና ካደራጃቸው አካል ስድስት ወር ያልሞላው የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ በነፃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የመንግስት ግዢ አስተዳደር ቡድን ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

6.     የአሸናፊው ድርጅት CPO ተመላሽ የሚሆነው የውል ማስከበሪያ የአጠቃላይ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% ሲያሲዝ ብቻ ነው።

7.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከመስሪያ ቤቱ በገዙት ዋጋ ማቅረቢያ ብቻ በግልጽ እና በሚታይ መልኩ ያለ ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን በተለያ የፖስታ በማሸግ ሁለት ፖስታ በአንድ ላይ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) የሥራ ቀናት እስከ 1130 ሰዓት ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

8.     በአስራ አንደኛው (11) የስራ ቀን ከጠዋቱ 230 እስከ 400 ሰዓት ተጫራጮች ሰነድ በማስገባት 400 ሰዓት ላይ ታሽጎ ልክ 430 ሰዓት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሁለተኛ ፎቅ ጨረታው ይከፈታል።

9.     /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ አድራሻ ከቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደር ህንፃ ላይ ሁለተኛ ፎቅ መጠየቅ ይችላሉ።

 

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ /ቤት

Save Tender