በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ የኤሌክትሪክዕቃዎች፣ ኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ቶንዶስ ፣አልባሳት፣ተሸከርካሪ ፣ጫማ እና ወንበር /office chair/ በግልፅ እንዲሁም ጫማ፣ የምግብ ጨው እና dorco/ምላጭ/ በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር C-02/2019
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ የኤሌክትሪክዕቃዎች፣ ኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ቶንዶስ ፣አልባሳት፣ተሸከርካሪ ፣ጫማ እና ወንበር /office chair/ በግልፅ እንዲሁም ጫማ፣ የምግብ ጨው እና dorco/ምላጭ/ በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡
1) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋርተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስከር ወረቀት (ከሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል፡፡
2) የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊዮን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርትፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡
3) በጨረታ የሚሸጠው ዕቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
4) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
5) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይየተገለፁትን በኢንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
6) የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሐራጅ ጨረታው 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል፡፡
7) ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመከፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡
8) ተጫራቾች ለዕቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታከስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡
9) ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ ዕቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
10) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ ዕቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሐራጅ ጨረታ የዕቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እንዲሁም የዕቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን ብር በታች ለሆነ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000 (መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
1) መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ስተጨማሪ ማብራሪያ - በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
