በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
1.የተለያዩ፣ የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ግርግዳ ላይ የሚታሰር የእንጨት ፋይል መደርደሪያ፣ የአይሲቲ ዕቃዎች፣የቢሮ ፈርኒቸሮች ጥገና፣የአይሲቲ ዕቃዎች ጥገና፣የመስተንግዶ አገልግሎት፣የህትመት አገልግሎት የዲኮር እና የዲጄ አገልግሎት፣የጉልበት ስራ አገልግሎት፣ የትራንስፖርት ኪራይ አገልግሎት፣የጀነሬተርጥገና እና የብረታብረት ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1.1.1. ተጫራቾች በመንግስት ግዢ በዕቃ አቅራቢነት ውስጥ የተመዘገቡ እና የግብር ከፋይመለያ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
1.1.2. ተጫራቾች እኛ ከሰጠነው የጨረታ ሰነድ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ ሞልቶ የሚያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
1.1.3. ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ሠነድ /ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
1.1.4. ተጫራቾች ከስር ከተጠቀሱት ሎቶች ውጪ ለእያንዳንዱ ሎቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አጠቃላይ ያቀረቡትን ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
1.1.5. ለመስተንግዶ አገልግሎት፣ለህትመት አገልግሎት፣ለትራንስፖርት አገልግሎት፣ለጥገና አገልግሎት፣ለጉልበት ስራ አገልግሎት፣ለዲጄ አገልግሎት እና ለብረታብረት ስራ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
1.1.6. ለግርግዳ ፋይል መደርደሪያ ስራ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንከ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
1.1.7. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የውሉን 10%ማስያዝ ይኖርበታል
1.1.8. ገዢው መስሪያ ቤት በጨረታው ወቅት 25% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል ፡፡
1.1.9. በተጨማሪም ገዢው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ 20 % እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ሊጨምር ይችላል፡፡
1.1.10. ተጫራቾች በተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው ::
1.1.11. ተጫራቾች ናሙናቸውን ከጨረታ መክፈቻው በፊት ማሥግባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች
1.1.12. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
1.1.13. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብርብቻ) በመክፈል በቂ/ክ/ከ/የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ፡፡
1.1.14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
1.1.15. ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡትን ዋጋ የሚቆይበትን ጊዜ ቢያንስ ለ 60 ቀን መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
1.1.16. ጨረታው በክኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ተጫራቾች ወይም ህግዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቂ/ክ/ከ/የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡
1.1.17. የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰብያ
በአ/አ/ከ/አስ/የመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 17/2002 አንቀፅ 17 ንዑስ 2 እና የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2002 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀፅ 20.5 በተደነገገው መሰረት ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የጨረታ ሰነድ በነፃ የምንሰጠው በሃገርውስጥ ምርት ማምረት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ስበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 011-515-88-38
አድራሻ፦ ብሄራዊ ከበድሉ ህንጻ በስተጀርባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አዲስ አበባ
