Tender Detail

Tender Details


ፀሐይ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች ለተገለጹት የስራ ዓይነቶች የሰው ኃይል በማቅረብ አግባብ ካለው ፈቃድ ሰጪ የመንግስት ተቋም ሙያዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በማወዳደር የሠራተኛ አቅርቦት ግዢ ማከናወን ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፀባ/003/2018

ፀሐይ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች ለተገለጹት የስራ ዓይነቶች የሰው ኃይል በማቅረብ አግባብ ካለው ፈቃድ ሰጪ የመንግስት ተቋም ሙያዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በማወዳደር የሠራተኛ አቅርቦት ግዢ ማከናወን ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ የስራው/የአገልግሎቱ ዓይነት
1 ለባንኩ ሁሉም ቅርንጫፎች የጽዳት ሰራተኛ አቅርቦት /ከነመስሪያ ግብዓቶቹ/
2 መኪና አጣቢ
3 የጉልበት ሰራተኛ

 

በጨረታው የሚወዳደሩ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ከሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የቅጥር/employment/ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶቹ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቅጅ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን የምስክር ወረቀት እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ከግብር ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ ሶስት መቶ ብር /300.00/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 9፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ የሚሆን ብር 50‚000.00 በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ዋስትናውም ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሊሆን ይገባዋል፡፡
  6. የጨረታው መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  7. ተጫራቾች በስራው/ዘርፉ ለ2 ዓመታትና ከዚያ በላይ የቆየ መሆን አለበት፤ ከሁለት ዓመት በታች ልምድ ያለው ድርጅት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

  • በስልክ ቁጥር +251 11 4 70 60 33 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ፣ መዓዛ ደሳለኝ ህንፃ 5ኛ ፎቅ የባንኩ ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
Save Tender