በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ሎት-1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት 2- የተለያዩ ፅዳት ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁፕር፡- አግጨ/009/ኦኩስፋ-2/2018 ዓ.ም
1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ሎት-1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት 2- የተለያዩ ፅዳት ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ60 ቀን የባንክ ዋስትና /BID BOND/ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር/supplier List ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን አየር ላይ ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል። የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም ሎት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓትበፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኃላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተመለከተው ነው፡-
1. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነአ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ አንደኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 1371/103 ውስጥ
ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85 ወይም 09-86-86-27-66
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት የማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) በሲ.ፒ.ኦ. ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
7. የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ነው።
8. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።
9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው።
10. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
Tel-0940209464
ሀይል ውሃ
አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ
Tel: 09-91-14-94-85 ወይም 09-86-86-27-66
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
